ሶስቱ መሰረቶች

ሶስቱ መሰረቶች

图书与工具书 | Abdulsemed

在電腦上使用BlueStacks –受到5億以上的遊戲玩家所信任的Android遊戲平台。

網頁修改於: 2019年9月1日

Play ሶስቱ መሰረቶች on PC

الأُصُولُ الثَّلاثَةُ
ሶስቱ መሰረቶች

ሸይኽ
ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወህሃብ
ረሒመሁላህ
(1115 – 1206 ዓ.ሂ.)

መግቢያ

“አልኡሱሉ አሥሠላሣህ” እና “አልቀዋዒዱል አርበዕ” ኪታቦች በሱንኒው አለም ባሉ ሙስሊሞች ዘንድ ሰፊ እውቅና እና ተቀባይነት ያላቸው ኪታቦች ናቸው፡፡ ኪታቦቹ በውስጣቸው ከያዙት አንገብጋቢ የተውሒድ መልእክት በተጨማሪ አቀራረባቸው በራሱ እራሱን የቻለ ትልቅ ስርኣተ-ትምህርት ነው፡፡ እያንዳንዱ ነጥብ በቁርኣናዊ ወይም ሐዲሣዊ ማስረጃ መደገፉ በዚህ ስርኣተ- ትምህርት ውስጥ ያለፈ ትውልድ የትኛውንም እምነት ነክ ጉዳይ ያለ ማስረጃ ሊቀበል እንደማይገባው ፅኑ መልእክት አለው፡፡
በትርጉም ስራዬ ላይ በኪታቦቹ ውስጥ የተጠቀሱ የቁርኣን አንቀፆችን፣ ሐዲሦችን እና የዑለማእ ንግግሮችን መገኛቸውን ያሰፈርኩ ሲሆን ሐዲሦቹን ቡኻሪና ሙስሊም ከዘገቧቸው ውጭ ባሉት ላይ የታላቁን ሙሐዲሥ የሸይኹል አልባኒን ብይኖች አስፍሬያለሁ፡፡ አልፎ አልፎ ሀሳቦችን ያብራራሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ማስታወሻዎች ከግርጌ አስፍሬያለሁ፡፡
ኪታቦቹን ለመማር ማስተማር ይበልጥ እንዲያግዝ በማለም ሙሉ ትርጉም ብቻ ከማድረግ ይልቅ ዐረብኛውን መልእክት ካሰፈርኩ በኋላ ቀጥሎ ትርጉሙን ያስከተልኩ ሲሆን ለጀማሪዎች እንዲያግዝ በማሰብም የዐረብኛ አናባቢ ምልክቶች (ሐረካት) እንዲኖሩ አድርጌያለሁ፡፡
ያለንበት ዘመን እንደ አሕባሽ ያሉ የጥፋት ሃይሎች ኢስላማችንን ለመናድ፣ ህዝባችንን በብልሹ እምነቶች ለመበከል ቆርጠው የተነሱበት ዘመን እንደመሆኑ ወላጆች ለልጆቻቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሊሰጡ የሚገባቸው ጊዜ ነው፡፡ ሁሌ እንደ አሸን እየፈሉ ያሉ የአስተሳሰብ ወረራዎችን ለመመከት ንቃተ-ህሊናን ማዳበር ቀዳሚው ምርጫ እንደመሆኑ ወላጆች ይህንን የትልቅ ዓሊም ትልቅ ስራ እና መሰል ጤናማ ኪታቦችን እየመረጡ ለልጆቻቸው በማቅረብ ልጆች ከምንም በላይ፣ ከምንም ቀድሞ የጌታቸውን ሐቅ እንዲያውቁ ሊያግዟቸውና እራሳቸውን ከጥፋት የሚጠብቁበት እውቀት ሊያስታጥቋቸው ይገባል፡፡ ዛሬ ላይ ለተውሒድ ግንዛቤውና ፍቅሩ ያለው ትውልድ ማፍራታችን በሂደት ጠንካራ ህዝብ ለመገንባት ፅኑ መሰረት ይሆነናል፡፡
መፅሐፉ በቀጣይ እትም በተሻለ መልኩ ይወጣ ዘንድ እርምት ወይም ሀሳብ ያለው ሰው ለሚሰጠኝ ጥቆማ አስቀድሜ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡


ሙሐመድ አሕመድ ሙነወር


ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወህሃብ አላህ ይዘንላቸውና በ 1115 ዓመተ-ሂጅራ ተወልደው በ 1206 ነው የሞቱት፡፡ ቁርኣንን ገና አስር አመት ሳይሞላቸው የሐፈዙ ሲሆን ዒልም ፍለጋ ከትውልድ ቀያቸው በመውጣት ወደ መካ፣ መዲናህ፣ አልአሕሳእ፣ በስራ፣ በግዳድ ተጉዘዋል፡፡ የተወለዱትም የሞቱትም ዑየይናህ ውስጥ ነው፣ በሳዑዲ ዐረቢያ ነጅድ ክልል፡፡ ለደዕዋ የሚያግዛቸውን እውቀት ከገበዩ በኋላ በቀጥታ ወደ ደዕዋው መስክ በመግባት ህይወታቸውን በዚሁ ላይ አሳልፈዋል፡፡ የደዕዋቸው ቀዳሚ ትኩረትም በዘመናቸው በሰፊው የተንሰራፋውን በኢስላም ስም የሚፈፀም የባእድ አምልኮ መጋፈጥ ነበር፡፡ የተውሒድ ዘመቻቸው በአላህ እገዛ ፍሬ አፍርቶ የልፋታቸውን ውጤት በአይናቸው ለማየት በቅተዋል፡፡
ሸይኹ ዐቂዳን ማስተካከል ላይ ያነጣጠሩ በርከት ያሉ ኪታቦችን ጥለው ያለፉ ሲሆን ተማሪዎቻቸውና ወራሾቻቸውም ሀላፊነታቸውን ተረክበው የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡
ሸይኹ - አላህ ይዘንላቸውና - ጠላቶቻቸው እንደሚቀጥፉባቸው ከቁርኣንና ከሐዲስ ያፈነገጠ እንግዳ አስተሳሰብ አላመጡም፡፡ ለእያንዳንዱ ንግግሮቻቸው የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃ መጥቀሳቸውም ይህንን ሐቅ በሚገባ ያስረዳል፡፡ በየመሀሉ የቀደምት ዑለማዎችን ንግግሮች ጣል ማድረጋቸውም በቀደምቶቹ ፍኖት ላይ የሚጓዙ እንጂ አዲስ አስተሳሰብ ጠንሳሽ እንዳልሆኑ በቂ ምስክር ነው፡፡

在電腦上遊玩ሶስቱ መሰረቶች . 輕易上手.

  • 在您的電腦上下載並安裝BlueStacks

  • 完成Google登入後即可訪問Play商店,或等你需要訪問Play商店十再登入

  • 在右上角的搜索欄中尋找 ሶስቱ መሰረቶች

  • 點擊以從搜索結果中安裝 ሶስቱ መሰረቶች

  • 完成Google登入(如果您跳過了步驟2),以安裝 ሶስቱ መሰረቶች

  • 在首頁畫面中點擊 ሶስቱ መሰረቶች 圖標來啟動遊戲

觀看影片